የቱርኩ ፕሬዝደንት የምእራባዊያን የጦርነት ጉሰማ ነገሮችን ያከፋል የሚል ስጋት እንዳላቸው አሳሰቡ፡፡

የኔቶ ቃልኪዳን አባል የሆነችው ቱርክ ፕሬዝደንቷ ረሲብ ጠይብ ኤርዶሃን ከዩክሬን እና ሩስያ ጋር በተያያዘ የሚደረገው የአውሮፓዊያን እንቅስቃሴ ጉዳዩ እንዲከፋ ያደርጋል ብለዋል፡፡

የአውሮፓዊያን አያያዝ ነገሩን ከማርገብ ይልቅ የማራገብ መሆኑም ያሰጋኛል ያሉት ኤርዶጋን መፍትሄ ማምጣት ላይ እንዲሰሩም ተማጽነዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በሙት ባህር ቀጠና ላይ ቀውስ መነሳቱን በፍጹም እንደማትሻ ስታስታውቅ የቆየችው ቱርክ በፕሬዝደንቷ በኩል ሁለቱን ሃገራት የማደራደር ፍላጎት እንዳላትም አስታውቃለች፡፡

ኤርዶጋን የሁለቱን ሃገራት መሪዎች ለማወያየት ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው መሆኑንም ያስታወቁ ሲሆነ ለዚህም ለሁለቱም ሃገራት መሪዎች ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

የሞስኮው ክሬምሊን ቤተመንግስት ቃልአቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ጥሪው እንደደረሰ እና ፑቲን ቱርክን እንደሚጎበኙ ያስታወቁ ሲሆን ውይይቱን ሩስያም ድጋፏን እንደምትሰጥ ጠቁመው ባለው ሁኔታ ግን አዳጋች ነው ሲሉ ማስረዳታቸውን አር ቲ ዘግቧል፡፡

አብዱልሰላም አንሳር
ጥር 28 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *