ሴኔጋል የአፍሪካን ዋንጫ ድል ለማክበር ሰኞን ብሄራዊ በዓል ስትል አወጀች።

የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድናቸው በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ ማሸነፉን ተከትሎ ሰኞ የህዝብ በዓል እንዲሆን ሲሉ ማወጃቸውን የሀገሪቱ ቴሌቪዥን አስታወቀ።

ፕሬዝዳንቱ በግብፅ እና በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉዞ ሲያጠናቅቁ ኮሞሮስን ለመጎብኘት አቅደው የነበር ቢሆንም በድል አድራጊዎቹ አናብስት ምክንያት ወደ ዳካር ተመልሰዋል ሲል RTS ዘግቧል።

በእሁዱ የካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ሴኔጋል በሊቨርፑሉ ኮከብ ሳዲዮ ማኔ መሪነት የመሀመድ ሳላህ ግብፅን 4-2 አሸንፋለች።

ጨዋታው ከተጨማሪ ሰዓት በኋላ ጎል ሳይቆጠርበት ተጠናቋል።

በ2002 እና 2019 ሴኔጋል ካለፉት ሁለት የፍጻሜ ሽንፈቶች በኋላ የመጀመሪያዋን የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ሆናለች።

አናብስቱ ማክሰኞ ዳካር በሚገኘው ፕሬዝዳንታዊ ቤተ መንግስት ትልቅ ድግስ ይጠብቃቸዋል ሲል RTS ቴሌቪዥን ተናግሯል።

ያይኔአበባ ሻምበል
ጥር 30 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.