የኔይማር አልጋ ወራሽ

የ15 ዓመቱ ብራዚላዊ በመላው አውሮፓ የበርካታ ክለቦችን ትኩረት ስቧል፡፡

ጥር 19 በብራዚል የወጣቶች ውድድር የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ፓልሜይራስ እና ኦኢስቴ ግጥሚያቸውን ለማከናወን አሟሙቀው ሲጨርሱ የባርሴሎና ፣ አርሰናል ፣ ሊቨርፑል ፣ ማንቸስተር ሲቲ ፣ ሳውዛምፕተን ፣ አያክስ እና ቤንፊካ መልማዮች ቦታቸውን ያዙ፡፡

ብዙዎቹ በስፍራው የተገኙት ኤንድሪክን ለመመልከት ሲሆን የ15 ዓመቱ ተጫዋች ከ21 ዓመት በታች ውድድሩን ወደ ሌላ ምዕራፍ አሸጋግሮታል፡፡

እስከ ሩብ ፍጻሜው አራት ጎሎችን አስቆጥሯል፤ የብራዚል እና ፒ.ኤስ.ጂው ኮከብ በእርሱ ዕድሜ ካሳረፈው ተጽዕኖ በላይ አበርክቷል፡፡

ቀጥሎ የተመለከቱት ነገር ይከሰታል ብለው ግን ፈጽሞ አላሰቡም፡፡

በጨዋታው 13ኛ ደቂቃ ላይ ከፓልሜይራሱ ታዳጊ ጀርባ ኳሷ ነጠረች፤ ለአፍታ እንኳን ሳያስብ ከፍጹም ቅጣት ምት ሳጥኑ ውጪ በ‹‹መቀስ ምት›› ወደ ጎሉ ላካት፤ ኳሷ ውብ በሆነ መልኩ መረብ ላይ አረፈች፡፡

ጋሪ ሊኒከር ‹‹ የተለየ ባለተሰጥኦ ብቅ እያለ መሆኑን የተመለከትን ይመስለኛል›› ብሏል፡፡

በድንገት ከብራዚላዊው ታሪካዊ ተጫዋች ሮናልዶ ጋር መነጻጸር ጀምሯል፡፡ ከሃገሪቱ ሌሎች ትልልቅ አጥቂዎች ጋር የሚያነጻጽሩትም ሞልተዋል፡፡

ኤንድሪክ በፍጻሜው ሳንቶስን 4ለ0 ሲያሸንፉም ኳስ እና መረብ አገናኝቷል፣ በውድድሩ ከፍ ያለ ዋጋ የሚያወጣ ተጫዋች ተብሎም ተመርጧል፡፡

አቤል ጀቤሳ
የካቲት 01 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *