የግሎባል ቴሌቭዥን ኔትወርክ ኦፍ አፍሪካ GTNA በ3 ቢሊየን ብር መነሻ ካፒታል በቅርቡ ስርጭት እንደሚጀምር ተገለጸ፡፡

ግሎባል ቴሌቭዥን ኔትወርክ ኦፍ አፍሪካ GTNA በኢትዮጵያ አነሳሽነት እና በሁሉም የአፍሪካ ሃገራት ጠንካራ ትብብር በ3 ቢሊየን ብር መነሻ ካፒታል፤ መቀመጫውን ኢትዮጵያ በማድረግ በቅርቡ ስርጭት እንደሚጀምር የGTNA መስራች ጋዜጠኛ ግሩም ጫላ በዛሬው እለት በስካይ ላይት ሆቴል ባደረገው ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግሯል፡፡

”አፍሪካን ለአለም “ በሚል መሪ ቃል የአፍሪካን ትርክት እና ትክክለኛ ማንነት ለአለም ለማስተዋወቅ ይህን የሚዲያ ተቋም ማቋቋም አስፈላጊ በመሆኑ ሁሉም የአፍሪካ ሀገራት አለም ስለ አህጉራችን ያለውን የተሳሳተ አመለካከት ለመቀየር እና ከዘመናዊ የባርነት እስራት ለመውጣት ይህን አጋጣሚ በመጠቀም በጋራ ሊታገሉ እንደሚገባ ጋዜጠኛ ግሩም ተናግሯል፡፡

ከ13 እስከ 15 የሚሆኑ የሚዲያ አካላት በጋራ ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው ሲሆን፣ ካሜሮን፣ ደቡብ አፍሪካ እና ዙምባዌን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ ሚዲያዎች ይኙበታል ተብሏል፡፡

በአሜሪካ ኒዮርክ ፤ በቻይና ቤጂንግ የሚገኙ ደግሞ ከአፍሪካ ውጪ በጋራ ለመስራት ፍቃደኛ የሆኑ አለም አቀፍ ሚዲያዎች ናቸው፡፡

GTNA ለዋና መስሪያ ቤትነት ግንባታ የሚሆን 5 ሺ ካሬ ሜትር መሬት ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የተረከበ ሲሆኑ፤ 30 ሚሊዮን ብር ለመሬቱ ክፍያ መፈጸሙን ተናግረዋል፡፡

በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው ይህ የሚዲያ ተቋም በአለም አቀፍ ደረጃ ተሰሚ በመሆን፤አፍሪካን ለአለም ለማሳወቅ ሁሉም የአፍሪካ ሃገራት በጋራ የሚሰሩበት ሊሆን እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ላይ መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡

መሳይ ገ/መድህን
የካቲት 01 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.