በአፍሪካ በ70 አመት ውስጥ 205 ያህል መፈንቅለ መንግስት ተደርገዋል፡፡

የፖለቲካ ተመራማሪዎች መዝገበው እንደያዙት ባለፉት 70 ዓመታት በጠቅላላ 205 መንግሥታትን በኃይል ለመገልበጥ የተደረጉ ሙከራዎች ነበሩ።

የፖለቲካ ተመራማሪዎች የሆኑት አሜሪካውያኑ ጆናታን ፖዌል እና ክላይተን ቲይን ፖውል እና ክላይተን መፈንቅለ መንግሥት ስኬታማ ነው የሚባለው ለ7 ቀናት ያክል መቆየት ከቻለ ነው ይላሉ።

እስካሁን በአፍሪካ 105 ያልተሳኩ እና 100 የተሳኩ መፈንቅለ መንግሥቶች ተካሂደዋል።

ምዕራባዊቷ አፍሪካ ሃገር ቡርኪና ፋሶ 7 የተሳኩ መፈንቅለ መንግሥቶች በማስተናገድ ትመራለች።

በእርግጥም አፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥቶችን አስተናግዳለች፤ ነገር ግን በኃይል የሚደረጉ የመንግሥት ለውጦች እየቀነሱ ነው።

ከ1960 እስከ 2000 (እኤአ) ባሉት 40 ዓመታት ውስጥ የተካሄዱ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራዎች መጠን በሚገርም ሁኔታ ተመሳሳይ ነው።

በዚህም በየአስር ዓመቱ 40 የሚጠጉ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራዎች ተደርገዋል።

ከዚያ በኋላ ግን ቁጥሩ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል። በ2000 የመጀመሪያ አስር ዓመታት ውስጥ 22 ሙከራዎች የተደረጉ ሲሆን ባለንበት አስር ዓመታት ውስጥ ግን ቁጥሩ 17 ደርሷል።

ሃገራቱ ነጻ ከወጡ በኋላ የገጠማቸውን አለመረጋጋት በመጥቀስ የመፈንቅለ መንግሥቱ አሃዙ ብዙም የሚያስደንቅ እንዳልሆነ ጆናታን ፓወል ይናገራል።

“የአፍሪካ ሃገራት ድህነትና የተዳከመ ኢኮኖሚን የመሳሰሉ ለበርካታ መፈንቅለ መንግሥቶች መፈጠር አመቺ የሆኑ ሁኔታዎች ይስተዋላሉ።

በተጨማሪም አንዲት ሃገር አንድ መፈንቅለ መንግሥት ካስተናገደች ሌሎች መፈንቅለ መንግሥቶች ተከትለው መከሰታቸው የተለመደ እንደሆነ ነው በምሁራኑ የተገለጸው፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
የካቲት 02 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *