የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በአማራ እና አፋር ክልሎች ከ1.64 ቢሊየን ብር በላይ ውድመት ገጥሞኛል አለ::

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባደረገው ጥናት በአማራ እና አፋር ክልሎች ከ1.64 ቢሊየን ብር በላይ ውድመት ገጥሞኛል ሲል ገለፀ::

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በአማራ እና በአፋር ክልሎች የጥገና ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን አስታውቋል::

ተቋሙ መሸጥ ከነበረበት ከ231ሚሊየን ብር በላይ ኪሳራ ገጥሞኛል ሲል አስታውቋል::

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን በሰጡት መግለጫ ጥናቱ ትግራይ ክልልን ያላጠቃለለ መሆኑን ገልፀው በቀሪ አካባቢዎች ከደህንነት ስጋት ነፃ በሆኑበት ጊዜ አስፈላጊው የጥገናን ስራ እንደሚያከናውን አስታውቋል

ተከዜና አሸጎዳ የሃይል ማመንጫ በምን አይነት ሁኔታ ላይ እንዳለ አላውቅም ያለው ኤሌክትሪክ ሃይሉ ተከዜን ጉዳት እንዳልደረሰበት ግን ጠቁሟል::

ሰራተኞቼ ላይ የከፋ ጉዳት አልደረሰም ሲል ገልጧል የኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ ኃይል

በራሴ ፋይናንስ የጥገና ስራው ተሰርቷል ያለው ተቋሙ 53 ከመቶ የሚሆኑት ጥገናዎች አስተማማኝ በሚባል ደረጃ ላይ እንደማይገኙ አስታውቋል::

አብዱልሰላም አንሳር
የካቲት 02 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *