የሊቢያው ጠቅላይ ሚኒስትር ከግድያ መትረፋቸው ተሰማ፡፡

በርካታ የፖለቲካ እና ማህበራዊ ቀውስ ላይ የምትገኘውን ሊቢያን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የሚመሯት አብዱልሀሚድ ድቤይባህ ሃገሪቱን 1 አመት ለሚጠጋ ጊዜም እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡

ከየትኛውም ፖለቲካ ፓርቲ ጋር ያልወገኑት እኚህ ጠ/ሚኒስትር ከተሞከረባቸው ግድያ መትረፋቸው ታውቋል፡፡

ወደቤታቸው በማምራት ላይ ሳሉ ለተሰነዘረባቸው ጥቃት ሃላፊነቱን ወስዳለው ያለ አካል ባይኖርም በሃገሪቱ ከቀጠለው ፖለቲካዊ ቀውስ ጋር በተያያዘ ስለመሆኑም ታውቋል፡፡

ለመገናኛ ብዙሃን ቃላቸውን የሰጡ የአይን እማኞች የታቀደ የግድያ ሙከራ እንደነበር የገለፁ ሲሆን በጉዳዩ ዙሪያ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን የሊቢያ ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የተደረገው የግድያ ሙከራው ተሳክቶ ቢሆን ኖሮ ቀድሞውኑ ፓለቲካል ቀውስ ውስጥ የሚገኘውን የሃገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ ይበልጠ እንዳያባብሰው በበርካቶች ስጋትን ጭሯል፡፡

እርሳቸውን ለመተካት ተይዞ የነበረን የምርጫ ቀጠሮ ቸል በማለታቸው የተሞከረባቸው እንደነበር የተጠቆመ ሲሆን ሊቢያ ዛሬ ላይ በምእራብ እና ምስራቅ ወገን ጦር ባነገቡ ሃይላት ጉተታ ውስጥ ትገኛለች፡፡

አብዱልሃሚድ የናጠጡ ባለፀጋ እና ገለልተኛ ፖለቲከኛ ሲሆኑ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆኑ ለማገልግል በቦታው ሲሰየሙ ብሄራዊ መግባባትን እና የምርጫ ሂደቶችን ያመቻቻሉ ተብሎ ነበር፡፡

አብዱሰላም አንሳር
የካቲት 03 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.