የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን በሚመለከት በስርአተ ትምህርት ውስጥ ተካቶ ሊሰጥ ነው

የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን በሚመለከት በመደበኛ ትምህርት ካሪኩለም ውስጥ ተካቶ ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተግባራዊ ሊደረግ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ትምህርት ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ እንዲሁም በስፖርት የማሰልጠኛ ማዕከላት መደበኛ የስፖርት ስልጠና ካሪኩለም ውስጥ እዲካተት ተደረጎ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ተቀርጿል፤ በቀጣዩ ዓመት ወደ ሥራ ይገባል ተብሏል።

የኢትዮጵያ የፀረ- አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ዋና ዳይሬከተር አቶ መኮንን ይደርሳል የስፖርት አበረታች ቅመሞችን የሚመለከቱ ጉዳዮች በመደበኛ ስርአተ ትምህርት ውስጥ እንደሚካተቱ የገለፁ ሲሆን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

የስፖርት አበረታች ቅመሞችን የሚመለከቱ ጉዳዮች በመደበኛ ትምህርት ካሪኩለም ውስጥ መካተቱ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ከማምጣቱም በላይ ከስፖርት አበረታች ቅመሞች ነፃ የሆኑ ጤናማ ስፖርተኞችና ንፁህ ስፖርት ለማስፋፋት የሚረዳ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

ከስፖርት አበረታች ቅመሞች ነፃ የሆኑ ጤናማ ስፖርተኞች ተፈጥረውና ተፈጥሯዊ በሆነ መልኩ ተወዳድሮ ማሸነፍ ባህል ለማድረግና ዶፒንግን በየደረጃው ለመከላከልና ለመቆጣጠር ባለስልጣኑ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ እየሠራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
የካቲት 07 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.