ህውሓት በአማራ ክልል ከተሞች በንፁሃን ዜጎች ላይ የግድያ ፣ የመድፈር እና የዘረፋ ጥቃችን ፈጽሟል አለ አምነስቲ

በሰሜን ኢትዮጵያ የአማራ ክልል ሁለት አካባቢዎች ከህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሀት) ጋር ግንኙነት ያላቸው ታጣቂዎች ሆን ብለው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ገድለዋል፣ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ሴቶችን እና ልጃገረዶችን በቡድን ደፍረዋል ፡፡

ከተደፈሩት ሴቶች መካከል ዕድሜያቸው ገና 14 ዓመት የሆኑ ልጃገረዶች እንደሚገኙበት ተቋሙ ዛሬ ባወጣው አዲስ ሪፖርት ገልጿል፡፡

ይህ ብቻ ሳይሆን የግል እና የህዝብ ንብረቶችን ዘርፈዋል ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል በዘገባ ው አስታውቋል።

እ.አ.አ በ2021 በነሀሴ ወር መጨረሻ እና በመስከረም መጀመሪያ በጭና እና ቆቦ አካባቢዎች በንጹሀን ላይ ግፉ የተፈፀመው የትግራይ ሃይሎች በሐምሌ ወር አካባቢዎቹን በተቆጣጠሩ ሰሞን ነው ይላል ሪፖርቱ።

ጥቃቶቹ በጭካኔ ድርጊቶች የተሞሉ ሲሆን ፣ የግድያ ዛቻዎች እና የብሔር ተኮር ስድቦችን የጥቃቱ አካል ናቸው፡፡

በቆቦ የአካባቢውሚሊሻዎች እና የታጠቁ ነዋሪዎች ያሳዩት የመከላከል ጥንካሬ ያበሳጫቸው የትግራይ ታጣቂዎች በሰላማዊው ህዝብ እልሃቸውን እየተወጡ ይመስላል።

“የትግራይ ሃይሎች ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች ሊከተሏቸው የሚገቡትን መሰረታዊ የአለም አቀፍ የሰብአዊ ህግ ደንቦችን ጥሰዋል ሲሉ በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ አፍሪካ፣ ቀንድ እና ታላላቅ ሀይቆች ምክትል ዳይሬክተር ሳራ ጃክሰን ተናግረዋል።

ከጁላይ 2021 ጀምሮ የትግራይ ሃይሎች በአማራ ክልል ስር በሚገኙ አካባቢዎች የጦር ወንጀል እና በሰው ልጆች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን የሚያሳዩ መረጃዎች እየጨመሩ መሆናቸውንም አንስተዋል ዳይሬክተሩ፡፡

‹‹አስገድዶ መድፈር ፣ ግድያ ፣ ዘረፋ እና ሆስፒታሎች ጨምሮ ተቋማትን ማቃጠል ይጨምራል” ሲሉ በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ አፍሪካ፣ ቀንድ እና ታላላቅ ሀይቆች ምክትል ዳይሬክተር ሳራ ጃክሰን ጨምረው ተናግረዋል።

“የህወሓት ባለስልጣናት እንዲህ አይነት ግፍ በአስቸኳይ ማስቆም እና በዚህ አይነት ወንጀል የተጠረጠረውን ሰውም ለፍርድ እንዲያቀርቡ ።” ጠይቀዋል

ያይኔአበባ ሻምበል
የካቲት 09 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.