በስድስት ወራት ብቻ 210 ዜጎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው አልፏል፡፡

በአዲስ አበባ ባለፉት ስድስት ወራት በተከሰቱ የትራፊክ አደጋዎች 210 ያህል ዜጎች ህይወታቸው እንዳጡ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በየጊዜው ጫናው የበረታው የትራፊክ አደጋ በሰው እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እያደረሰ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

በመዲናዋ ባለፉት ስድስት ወራቶች ብቻ 24ሺህ ያህል የትራፊክ አደጋዎች መከሰታቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም ከፖሊስ ኮሚሽኑ ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካው ፋንታ በተከሰቱ የትራፊክ አደጋዎች 210 የሞት አደጋ የተመዘገበ ሲሆን ከባድ የአካል ጉዳት 946 እንደዚሁም ቀላል የአካል ጉዳት ደግሞ 575 ነው፡፡

በንብረት ላይ ደግሞ 14ሺህ 168 ያህል አደጋዎች መከሰታቸውንም ኮማንደር ፋሲካው ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የተከሰተው የትራፊክ አደጋ በ5ሺህ ያህል መቀነስ እንዳሳየ ገልጸዋል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
የካቲት 09 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *