ከ ሁለት ሳምንት በፊት በመፈንቅለ መንግስት ፕሬዝዳንት ሮች ካቦሬን ከስልጣን ያወረደው ጁንታ መሪ ፖል ሄንሪ ሳንዳዎጎ ዳሚባ የቡርኪና ፋሶ ፕሬዝዳንት ለመሆን ቃለ መሀላ ይፈፅማሉ፡፡
ባለፈው ሳምንት ነበር የህገ መንግስት ምክር ቤቱ የካቦሬን መልቀቂያ በመቀበል ፣ የ 41 አመት ዕድሜውን ዳሚባን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት በማለት በይፋ የሾመው፡፡
የሀገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በአለ ሲመቱን ከህገ መንግስት ምክር ቤቱ ህንፃ በቀጥታ እንደሚያስተላልፍ ገልጧል፡፡
በሀገሪቱ ምስራቅና ሰሜን አቅጣጫ ችግር የሚፈጥሩትን አክራሪ ጂሀዲስቶች ማስወገድ የተሳናቸው Kaboré ለወራት ከዘለቀ የህዝብ አመፅ በኋላ ዳሚባና ያስከተሏቸው ወታደሮች ከሰልጣናቸው አውርደዋቸዋል፡
ቢቢሲ
ሔኖከ አስራት
የካቲት 09 ቀን 2014 ዓ.ም











