በብራዚል መዲና ሪዮ ዲጄኔሮ የተከሰተው ከባድ የጎርፍ አደጋ ቢያንስ የ 23 ሰዎች ህይወት ሳይቀጥፍ እንዳልቀረ የተገመተ ሲሆን በርካታ ንብረትም አውድሟል፡፡
በጣም ከተጎዱ አካባቢዎች ሰዎችን ማንሳቷን ያስታወቀችው ብራዚል ይህ ቢሆን እንኳን ያደረሰው ጉዳት ከተገመተው በላይ መሆኑንም ጠቁማለች፡፡
ብራዚል ከአደጋው መከሰት አስቀድማ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከአካባቢው ብታርቅም የጎርፍ አደጋው እና ጎርፉ ያስከተለው ከባድ የመሬት መንሸራተት የሟቾችን ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተገምቷል፡፡
አርቲ
አብድልሰላም አንሳር
የካቲት 09 ቀን 2014 ዓ.ም











