ቦርዱ ምርጫ ቦርድ 26 ፓርቲዎች በአንድ ወር ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርጉ ያሳሰበው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በትላንትናው እለት መነሳቱን ተከትሎ ነው፡፡
ኅዳር 23 ቀን 2014 ከፓርቲዎች ጋር ባደረገው ምክክር ከ6ተኛው አገራዊ ምርጫ መጠናቀቅ በኋላ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂዱና የሰነድ ማሻሻያ እንዲያደርጉ የተገለፀላቸው ፓርቲዎች የሚጠበቅባቸውን አጠናቀው ባለማቅረባቸው፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተነሳ በአንድ ወር ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤያቸውን እንዲያከናውኑ እና ለቦርዱ እንዲያስገቡ መወሰኑ በምክክሩ ወቅትም ለፓርቲዎች መገለጹን አስታውሷል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
የካቲት 09 ቀን 2014 ዓ.ም











