ኢትዮጵያ በአፍሪካ በኮቪድ 19 በተያዙ እንዲሁም በቫይረሱ በሞቱት ሰዎች ቁጥር አራተኛ እና አምስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

በኢትዮጵያ እስከ ዛሬዋ የካቲት 10 ቀን ድረስ በኮቪድ 19 ቫይረስ የተያዙ ዜጎች ቁጥር 467ሺህ 860 ሲሆን በቫይረስ የሞቱ ደግሞ 7ሺህ 428 ነው፡፡

በኢትዮጵያ ክትባቱን ሙሉ በሙሉ የወሰዱት 4ሚሊየን ብቻ ሲሆኑ የመጀመርያ ዙር ብቻ የተከተቡ ዜጎች ቁጥር ደግሞ 11ሚሊየን እንደሆነ ከጤና ሚኒስትር ያገኝነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 409ሺህ 240 ያህል ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል ተብሏል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ባለፈው ታኅሣሥ ወር እንዲሁ ተመሳሳይ የክትባት ዘመቻ ጀምሮ ከ5.5 ሚሊየን በላይ ዜጎችን መከተቡ አይዘነጋም።

አሁን ሀገሪቷያ በ10 ቀናት ውስጥ 20 ሚሊዮን ክትባቶችን ለዜጎች ለመስጠት 90 ሺህ የሰው ኃይል እንደተሰማራ አስታውቃለች፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ክትባት መስጠት ከተጀመረ ከ11 ወራቶች የተቆጠሩ ሲሆን እስካሁን ከ10 ሚሊየን በላይ ሰዎች የኮቪድ-19 ክትባት እንዳገኙ ነገር ግን በሚጠበቀው መጠን ሰዎች እየተከተቡ እንዳልሆነ ተገልጿል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
የካቲት 10 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *