የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው 17 አመት እስር ተፈርዶበት ከእስር አምልጦ የነበረው እስረኛ በከባድ ወንጀል ሲሳተፍ ተይዟል ፡፡
ከዚህ ግለሰብ በተጨማሪም ሌላ ወንጀለኛ በሌለበት 15 አመት እስር ተፈርዶበት እንደዚሁ በከፍተኛ ወንጀል ሲሳተፍ እጅ ከፍንጅ መያዙን ፖሊስ ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡
የኮሚሽኑ የህዝብ ግኑኝነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካው ፋንታ እንደተናገሩት በመዲናዋ የከባድ ወንጀል ከዚህ በፊት ከነበረው አንጻር ሲታይ 13 ከመቶ ያህል መቀነሱን ተናግረዋል፡፡
የከባድ ወንጀል አይነት ከሚባሉት መካከል በጦር መሳርያ የተደራጀ ዝርፍያ ፤ የመኪና ስርቆት እንደዚሁም ሰው የመግደል ወንጀል አይነቶች ናቸው ብለዋል፡፡
በስድስት ወራቶች ውስጥ ከተያዙ ወንጀለኞች መካከል አብዛኛዎቹ ከማረሚያ ቤት ያመለጡ እና የእስር ጊዜያቸውን ጨርሰው የወጡ ናቸው ተብሏል፡፡
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
የካቲት 10 ቀን 2014 ዓ.ም











