ባለፉት ስድስት ወራት የተገኘው ገቢ ከፍተኛ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ

ባለፉት ስድስት ወራት የተገኘው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ14.9 በመቶ እድገት ማሳየቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ተናግረዋል፡፡

ነገር ግን በበጀት ዓመቱ ባለፉት ስድስት ወራት 297 ቢሊየን ብር ወጪ ተደርጓል፤ ይህም ባለፉት ስድስት ወራት ወጪ ከተደረገው የ39 በመቶ እድገት አሳይቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አሕመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከፓርላማ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።
በስድስት ወራቱ ውስጥ የወጪ ንግድ 25 በመቶ አድጓል፤ ከዚህም ውስጥ የሸቀጥ ወጪ ንግድ 21 በመቶ ፣ አገልግሎት 27 በመቶ፣ ኢንዱስትሪ 25 በመቶ አድገዋል ብለዋል።

በአጠቃላይ ለ2 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የቀረበ ገቢ ከወጪ ንግዱ መገኘቱንም ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የገቢ ንግዱ 25 በመቶ አድጓል ። የምግብ ሸቀጥ፣ የነዳኝ እና የማዳበሪ ገቢ ማደግ ለገቢ ንግዱ መጨመር አስተዋፅኦ አበርክቷል።

በግማሽ ዓመቱ ውስጥ 1 ነጥብ 6 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንትን ሀገሪቱ ማግኘት ችላለች።

ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ23 በመቶ እድገት ያለው ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት የሚያድግበትን ፍጥነት “ያዝ” ማድረግ እንደሚያስፈልግ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ተናግረዋል።

“የአወላለድ ስርዓታችንን ትንሽ ያዝ ማድረግ ካልተቻለ ፍላጎት እየጨመረ ስለሚሔድ በከፍተኛ ሁኔታ አስቸጋሪ ይሆናል” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩንም ሆነ የምክር ቤቱን አባላት ፈገግ ባደረገው ጉዳይ ላይ ሲናገሩ “ወሊድ መቆጣጠር ማለት በብዙ መንገድ ስለሆነ በሚመቻችሁ መንገድ መቆጣጠር ይቻላል” ብለዋል።

ረድኤት ገበየሁ
የካቲት 15 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.