በአዲስ አበባ ከተማ 90 ከመቶ የሚሆኑ ተሽከርካሪዎች የእሳት ማጥፍያ መሳርያ የላቸውም መባሉን ሰምተናል፡፡

በመዲናዋ ከሚገኙ 1.3 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎች ውስጥ 90 ከመቶ በላይ የሚሆኑት የእሳትማጥፊያ እንደሌላቸው ኢትዮ ኤፍ ኤም ከእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሰምቷል፡፡

የትራንስፖርት ባለስልጣን መረጃ እንደሚያሳው በኢትዮጵያ ከ1.3ሚሊየን በላይ ተሽከርካሪዎች እንዳሉ የተገለጸ ሲሆን ከነዚህ መካከል 54 ከመቶ የሚሆኑት የአገልግሎት ዘመናቸው የተጠናቀቀ መሆኑን ነው፡፡

እነዚህ ያረጁ ወይም የአገልግሎት ዘመናቸው ያለፈ ተሽከርካሪዎች አደጋ የማስተናገዳቸው መጠን ከፍተኛ ነው የሚሉት የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ አብዛኛዎቹ የእሳት አደጋ መቆጣጠርያ መሳርያ አልገጠመላቸውም ብለውናል፡፡

አቶ ንጋቱ አክለው እንደተናገሩት እንደ ኤርፖርቶች ድርጅት፣የሸገር ባሶች፣ከኤምባሲዎች እና ከቤተ መንግስት ተሽከርካሪዎች ውጪ በከተማው የሚንቀሳቀሱ 90 ከመቶ የሚጠጉ ተሽከርካሪዎች የእሳት ማጥፍያ ወይም (fire extinguisher) አልተገጠመላቸውም ብለዋል፡፡

ተሽከርካሪዎቹ የቦሎ እድሳት በሚያደርጉበት ጊዜ ብቻ የእሳት ማጥፍያውን በኪራይ እንደሚጠቀሙ ነው የተገለጸው፡፡

የእሳት ማጥፍያው መሳርያ ገበያ ላይ ቢበዛ ከ800 ብር እንደማይበልጥ የጠቆሙት አቶ ንጋቱ 5ሚሊየን ብር የሚያወጣ ተሽከርካሪ ገዝተው 800 ማውጣት የከበዳቸው አሽከርካሪዎች አሉ ብለውናል፡፡

ሔኖክ ወ\ገብርኤል
የካቲት 17 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *