ተቋርጦ የነበረው የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት በወረዳዎች መስጠት ጀምሯል ፡፡

አገልግሎቱን ለማግኘትም የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ከሚኖሩበት ወረዳ መታወቂያውን ለማግኘት ወደሚያመሩበት ወረዳ የመሸኛ ማሰረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ተቋርጦ የሰነበተው አዲስ የነዋሪነት መታወቂያን የመስጠት አገልግሎት ከወረዳ ወረዳ በሚደረግ የመሸኛ አሰጣጥ ብቻ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚቻል ኢትዮ ኤፍ ኤም ከኤጀንሲው ሰምቷል፡፡

በአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገና እና መረጃ ኤጀንሲ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት አቶ መላክ መኮንን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቁት በያዝነው ሳምንት ተቋርጦ የነበረው የመታወቂያ ምትክ እና እድሳት አገልግሎት በሁሉም ወረዳዎች አገልግሎት መስጠት ጀምሯል ፡፡

ከዚሁ በተጨማሪ ተቋርጦ የሰነበተውና ከወረዳ ወረዳ በመሸኛ አማካኝነት ሲሰጥ የነበረው አዲስ የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት በዛሬው እለት መጀመሩን ነግረውናል፡፡

ይሁን እንጂ ከክልል ከተሞች የሚመጡ መሸኛዎችን በመቀበል የሚሰጠው አዲስ የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት ገና እንዳልተጀመረ የነገሩን አቶ መላክ አገልግሎቱን ከሳምንት በኋላ ለማስጀመር እየተሰራበት መሆኑን ነግረውናል፡፡

የውልሰው ገዝሙ
የካቲት 17 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.