ቱርክ ለሩስያም ሆነ ለዩክሬን ጀርባዋን እንደማትሰጥ አስታወቀች፡፡

የሃገሪቱ ፕሬዝደንት ረሲብ ታይብ ኤርዶሃን እንዳስታወቁት ከሆነ ቱርክ ለሩስያም ሆነ ለዩክሬን እንደማትወግን አስታውቀዋል፡፡

ፕሬዝደንቱ ከሁለቱም ጋር በጥብቅ ያስተሳሰረን ጥቅም አለን ያሉ ሲሆን ለማንኛቸውም እንደማይወግኑም ጠቁመዋል፡፡

የጥቁር ባህር ጎረቤቶቻችን ሲሉ የገለጹዋቸው ሩስያ እና ዩክሬን ሁሉንም ትተው ወደ ውይይት እንዲመለሱም ተማፅነዋል፡፡

ኤርዶሃን በአፍሪካ ሃገራት የነበራቸውን ጉብኝት አጠናቀው ሲመለሱ በሰጡት መግለጫቸው ይህንን ይበሉ እንጂ ቱርክ በቃል ኪዳኑ የታሰረችበት ኔቶ ዛሬም ዝግጅቱን እንደቀጠለ ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዩክሬን ያለው ቀውስ እየተባባሰ መምጣቱ እየተዘገበ ይገኛል የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዶንባስ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ መጀመሩን ይፋ ማድረጋቸውም እየተነገረ ነው፡፡

አብዱልሰላም አንሳር
የካቲት 17 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.