የዩክሬን ታጣቂ ሃይሎች በ3 DPR ሰፈሮች ላይ ከባድ መሳሪያ መተኮሳቸው የተነገረ ሲሆን በዚህም 2 ሰዎች ሲሞቱ 12 ያክሉ ደግሞ ቆስለዋል ሲሉ የDPR አካባቢ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
የዩክሬን ሃይሎች በሮስቶቭ ክልል ሚሎሮቮ የሚገኘውን ወታደራዊ አየር ማረፊያ ቶቺካ በተሰኘው ሚሳኤል መምታታቸውን ያልተረጋገጠ ዘገባዎች አመላክተዋል ሲል RT ኒውስ ዘግቧል፡፡
የዩክሬን ሃይሎች ከኪየቭ 70 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ያለውን ቁልፍ ድልድይ ማፈንዳታቸውንም ዘገባው አክሏል፡፡
በሁሉም የኪየቭ አካባቢዎችም በአንድ ሌሊት በርካታ ፍንዳታዎች ተዘግበዋል።
አውሮፕላንም ከህንጻ ጋር መጋጨቱና የቪታሊ ከንቲባን ጨምሮ ሶስት ሰዎች መቁሰላቸው ተነግሯል፡፡
ይህ ሁሉ እየሆነ ባለበት የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በቼርኖቤል በዋና ከተማዋ በኪየቭ እንደሚቆዩ አስታውቀዋል፡፡
ከ100,000 በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል ሲል የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ ማስታወቁን የሩሲያው አርቲ የዜና ወኪል ዘግቧል።
የውልሰው ገዝሙ
የካቲት 18 ቀን 2014 ዓ.ም











