ሩስያ ከዩክሬን ጋር መነጋገር እንደምትፈልግ አስታወቀች፡፡

የክሬምሊን ቃልአቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ልኡካን ወደ ቤላሩስ መዲና ሚንስክ እንደሚልኩ ያስታወቁ ሲሆን በልኡኩ ውስጥም የውጭ ጉዳይ ሚስትሩ ሰርጌ ላቭሮቭ እና የመከላከያ ሚኒስትሩን እና ሌሎችም ከፍተኛ ባለስልጣናት እንሚኖሩ አስታውቋል፡፡

ዩክሬን አስቀድማ መነጋገር እፈልጋለው ስትል የቆየች ቢሆንም ከ24 ሰአታት የበለጠን ወታደራዊ እርምጃ የወሰደችው ሞስኮ አሁን ላይ ወደ መነጋገሩ ማዘንበሏ ታውቋል፡፡

የዩክሬኑ ዘለንስካይ ለንግግር ዝግጁ መሆናቸውን ካስታወቁ በሁዋላ ዩክሬን ገለልተኝነትም ላይ መነጋገር እንደሚችሉ ጠቁመው ነበር፡፡

ፑቲን ይህ ሁሉ ያስፈለገው ቀጠናውን ከኔቶ አባልነት እና እንደርሳቸው አገላለፅ ከናዚያዊ አገዛዝ ለማላቀቅ ያለመ መሆኑን ተናግረው ሲል አር ቲ አስነብቧል፡፡

አብዱልሰላም አንሳር
የካቲት 18 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *