በኢንዶኔዢያ በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያንስ ሁለት ሰዎች መሞታቸው ተሰማ

6.2 ሬክተር ስኬል የተለካው ክስተቱ ሱማትራ በተባለች የኢንዶኔሲያ ግዛት መሆኑም ታውቋል፡፡

ከባድ የመሬት መንቀጥቀጡ ከ20የሚልቁ ሰዎች ላይ ጉዳት ሳያደርስ እንዳልቀረም ተዘገቧል፡፡

በቡኪቲንጊ ከተማ የተነሳው የመሬት መንቀጥቀጡ በከተማዋ እና በዙሪያዋ እስከ 66ኪሎ ሜትር ርቀት እንደተስተዋለም ታውቋት፡፡

ህንፃዎች መፈራረስ እና የመኖሪያ ቤቶች ላይም ጉዳት መድረሱ ታውቋል፡፡

በተመሳሳይ በጎረቤቶቿ ማሌዢያ እና ሲንጋፖርም የመሬት መንሸራተት መከሰቱ አር ቲ የተሰኘው የሩሲያ የዜና አውታር ዘግቧል፡፡

አብዱልሰላም አንሳር
የካቲት 18 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *