ለስድስት ቀናት በቀጠለው የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት 5 ሺህ 710 የሩስያ ወታደሮች መገደላቸውን የዩክሬን ወታደራዊ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።


ከ200 በላይ የሩስያ ወታደሮች በዩክሬን ጦር መማረካቸውን የሃገሪቱ ኤታማዦር ሹም ቃለ አቀባይ በፌስቡክ ባጋሩት የቪዲዮ መልዕክት አክለው ገልጸዋል።
ባለሥልጣኑ 198 የሩሲያ ታንኮች፣ 29 አውሮፕላኖች፣ 846 የታጠቁ ተሽከርካሪዎች እና 29 ሄሊኮፕተሮች መውደማቸውን ተናግረዋል፡፤
ቢቢሲ ግን ዩክሬን አድርሸዋለሁ ያለችውን ውድመት ከገለልተኛ ወገን ማረጋገጥ አልቻልኩም ብሏል፡፡
በሞስኮ የሚገኙ ባለስልጣናት ወታደሮቻቸው እንደሞቱና እንደተጉዱ ከቀናት ማቅማማት በኃላ ማመናቸው የሚታወስ ነው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩክሬን ሁለተኛ ትልቅ ከተማ ካርኪቭ ማዕከል በሩሲያ ሚሳኤል መመታቱን የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።
ፍሪደም አደባባይ የደረሰውን ፍንዳታ የሚያሳይ ቪዲዮ በትዊተር ገጻቸው ያጋሩ ሲሆን የሩስያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንንም በጦርነት ወንጀል ከሰዋል።
በዚህ ምክንያት 10 ሰዎች ሲገደሉ 20 ያህሉ እንደተጎዱ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ከሟቾቹ መካከል ሁለት የህንድ ዜግነት ያላቸው ተማሪዎች መኖራቸውን የህንድ የውጪ ጎዳይ ሚኒስትር ተናግሯል፡፡
በትላንትና እለት በነበረው ውጊያ 70 የዩክሬን ወታደሮች መገደላቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
የካቲት 22 ቀን 2014 ዓ.ም
ያይኔአበባ ሻምበል

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *