አፍሪካዊያን በዩክሬን ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸው ተነገረ፡፡

ዩክሬን ውስጥ የሚገኙ የውጭ ሃገር ዜግነት ያላቸው ዜጎች ወደ ጎረቤት ሀገራት ድንበር አቋርጠው መውጣት የተፈቀደላቸው ሲሆን አፍሪካዊያን ይህ እድል ተነፍጓቸዋል ተብሏል፡፡

በዩክሬን የሚገኙ አብዛኛዎቹ ተፈናቃዮች ወደ ፖላንድ ያቀኑ ሲሆን አፍሪካዊያን ግን እዛው ዩክሬን እንዲቆዩ ተገደዋል፤
በዚህ የተነሳም ዜጎቹ ጎዳና ማደሪያቸው አድርገዋል ሲል አልጀዚራ አስነብቧል፡፡

ይህንንም ተከትሎ የናይጄርያ መንግስት የአፍሪካዊያን መብት ሊከበር ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አፍሪካዊያን ችግር ባለባቸው ሀገራት መብታቸው እየተነፈገ እና ለችግር እየተጋለጡ ይገኛሉ ይህ አይነት አስተሳሰብ መለወጥ አለበት ሲሉ የናይጄርያው ፕሬዝዳንት ማማዱ ቡሀሪ ተናግረዋል፡፡

እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት ዩክሬንን ለቀው ወደ ፖላንድ የገቡ ዜጎች ቁጥር 286ሺህ ሲሆን ወደ ሃንጋሪ የገቡ ዜጎች ቁጥር ደግሞ 87ሺህ ይሆናሉ ተብሏል፡፡

ወደ ሞልዶቫ እና ሮማኒያ ያቀኑ ዜጎች ቁጥር ደግሞ 56ሺህ ይጠጋሉ ሲል አልጀዚራ አስነብቧል፡፡

ሔኖክ ወ\ገብርኤል
የካቲት 22 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *