ኮንቴይነር እጥረት እና የመርከብ ዋጋ መጨመር የሎጀስቲክስ ዘርፉ ላይ ጫና መፍጠሩን ሰምተናል

ለሎጀስቲክ ዘርፉ የውስጥ አቅም ማነስ ፣ የኮቪድ መከሰት ፣ የኮንቲነር እጥረት እና የመርከብ ዋጋ መጨመር ከባድ የሚባል ጫና ማሳደሩን የትራንፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ናቸው የገለጹት፡፡

ሚንስትሯ ይህን ያሉት ከተቋቋመ 4 አመታት የሆነው የሎጀስቲክስ ማህበር የመጀመርያው ጠቅላላ ጉባኤውን በሸራተን አዲስ ሆቴል ባደረገበት ወቅት ነው፡፡

የማህበሩ ፕሬዝዳንት የሆኑት ወ/ሮ ኤልሳቤት ጌታሁን እንዳሉት ዘርፉ ውስብስብ በመሆኑና ሁሉንም የስራ ዘርፍ የሚያካትት እንደመሆኑ መህበራቸው በቀጣይ 5 ዓመታት የተለያዩ የአሰራር ማሻሻያዎች በመስራ ዘርፉን ለማዘመን እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።

የትራንፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር የሆኑት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ በበኩላቸው ለሎጀስቲክ ዘርፉ የውስጥ አቅም ማነስ ፣ የኮቪድ መከሰት ፣ የኮንቲነር እጥረት ፣ የመርከብ ዋጋ መጨመር ከባድ የሚባል ጫና አሳድሮብናል ብለዋል።

ያም ሆኖ ግን ጥሩ የሚባል መሻሻል አለው ያሉት ሚኒስትሯ የዓለም ባንክ በትራንፖርት ዘርፍ ላይ ያወጣውን መስፈርት መሰረት በማድረግ እ.ኤ.አ. በ2016 ኢትዮጵያ ከ160 ሃገራት የነበረችበት ደረጃ 126 ተኛ ላይ እንደነበር አስታውሰዋል።

ሚኒስቴር መስርያ ቤታቸውም “የአለም ባንክ መስፈርቱን መሰረት በማድረግ በውስጥ አቅም በተሰራው መመዘኛ 114ተኛ ደረጃ ላይ ደርስናል ብለን እናስባለን” ሲሉ ተናግረዋል።

ረድኤት ገበየሁ
የካቲት 25 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *