የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለ10ኛ ዙር “የይቆጥቡ፣ይሸለሙ” የእጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት ዛሬ በግዮን ሆቴል አካሄደ።


ባንኩ ለሽልማት ያዘጋጃቸው በ1ኛ እጣ ሁለት የመኖሪያ ቤት አፓርትመንት፣ በ2ኛ የእጣ 10 ዘመናዊ አውቶሞቢሎች፣ በ3ኛ እጣ 30 ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎችና በ4ኛ እጣ 30 ላፕቶችን ናቸው።

በመርሐ ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንዳሉት፣ የእድገት ማማ ላይ የደረሱት አገራት የተሻለ የቁጠባ ባህል በማዳበራቸው በመሆኑ ህብረተሰቡ የቁጠባ ባህልን እያዳበረ እንዲሸለምም ጥሪ አቅርበዋል።


ንግድ ባንክም ህዝቡ የቁጠባ ባህል እንዲያዳብር ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ ባደረገው እንቅስቃሴ አመርቂ ውጤት አስመዝግቧል ብለዋል።መርኃ-ግብሩ ከ30 ሚሊዮን ደምበኞች በላይ የተሳተፉበት ሲሆን 72 ደምበኞች እድለኛ ሆነዋል።

መሳይ ገ/ መድህን
የካቲት 25 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *