እስራኤል 100 ሺ ለሚሆኑ ዩክሬናዊያን ዜግነት ልትሰጥ ነው ተባለ፡፡


የእስራኤል የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ጦርነቱን ሸሽተው ለወጡ 100,000 ለሚሆኑ ዩክሬናውያን የእስረኤል ዜግነት ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆኗን እስራኤል ታይምስ ዘግቧል።

እንደ እስራኤል ታይምስ ዘገባ ከሆነ ሻክድ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያየር ላፒድ ከጦርነቱ የሚያመልጡ ዩክሬናውያን የአንድ አመት የመኖሪያ እና የስራ ፍቃድ ለመስጠት አዲስ ፖሊሲ እያረቀቁ መሆናቸውን ገልጸዋል።


ሩሲያ ወረራዋን ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ 1,555 ዩክሬናውያን እስራኤል መግባታቸውን ሚንስተሩ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ 150 ያህሉ በህጉ መሰረት የእስራኤል ዜግነት ለማግኘት ብቁ መሆናቸው ገልጸው፤ የዜግነት አሰጥጡ በሌሎች ሃገራት በሚኖሩ አይሁዳዊያን ስደተኞች ላይ ያተኮረ ነው ቢባልም ፤ የዩክሬን ስደተኛ ዜጎችን ለመርዳትም እስራኤል ፍቀደኛ መሆኗን ተናግረዋል፡፡

መሳይ ገ/መድህን
የካቲት 28 ቀን፣ 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *