በሸማቾች በኩል ያለው የዘይት ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እየተሸጠ ነው፡፡

ቀደም ብሎ የገባው የዘይት ምርት በየመሸጫ ሱቆች ውስጥ በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ ተደራሽ የማድረጉን ሃላፊነት እየተወጣው መሆኑን የከተማው የህብረት ስራ ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ህብረት ስራ ኤጀንሲ የግብይት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ደብሪቱ ላለም ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ትክክለኛ ምክንያቱ ባልታወቀ መልኩ የተከሰተው የዘይት ዋጋ መናር በሸማች ማህበራቱ በኩል ቀደም ብሎ በገባው የዘይት መሸጫ ዋጋ ላይ ምንም አይነት ለውጥን አለማሳየቱን እና የአቅርቦት እጥረቱ ግን ቀደም ብሎም መኖሩን ነግረውናል፡፡

አሁንም ምርቱ በሚገኝባቸው መሸጫ ሱቆች ዋጋው ምንም አይነት ለውጥ እንዳልተደረገበት ነግረውናል፡፡

ባለፉት ቀናት አምስት ሊትር ዘይት በሸማች ማህበረቱ በኩል በሚቀርበው የእሁድ ገበያ አማካኝነት ከ 650- 700 ድርስ ሲሸጥ ነበር ሲሉም ነግረውናል፡፡

የኢንዱስትሪ፤ የግብርና እንዲሁም የባልትና ውጤቶች በ10 ዩኒየኖች አማካኝት ለ 148 ሸማች ስራ ማህበራት ተደራሽ የሚደርጉ ሲሆን እነዚህ ሸማች ማህበራትም በየወረዳው በአማካኝነት ከ7 እስከ 3 ያክል ሱቆች እንዳላቸው ወ/ሮ ደብሪቱ ነግረውናል፡፡

ሌሎች የግብርና ምርቶችን በተመለከተ በአነስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የከተማው ህብረት ስራ ኤጀንሲ እየሰራ መሆኑንም ነግረውናል፡፡

ይሁንና በአሁኑ ሰዓት የተከሰተውን የዘይት ዋጋ መናር ለመቆጣጠር ባለድርሻ አካላት ትኩረት አድርገው መስራት አላባቸው የሚሉት ወ/ሮ ደብሪቱ ህብረተሰቡንም ከዚህ ቀውስ መታደግ እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡

የውልሰው ገዝሙ
የካቲት 29 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.