በኮቪድ 19 ወረርሽኝ የሟቾች ቁጥር ከ 6 ሚሊዮን በላይ ማሻቀቡን ተገለጸ

በአለም አቀፍ ደረጃ በኮቪድ 19 የሟቾች ቁጥር ከ 6 ሚሊዮን መሻገሩን ዩፒአይ ድህረ ገጽ ዘግቧል፡፡

ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ካለፈው ሶስት አመት ጀመሮ ስርጭቱን እና በወረርሽኝ ሳቢያ እየደረሰ ያለውን የሞተ መጠን ላይ ጥናት ማካሄዱን ነው የተገለፀው፡፡

እንደጥናቱ ከሆነ በሶስት አመት ውስጥ በኮቪድ 19 ሳቢያ ከ6 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተው መሞታቸው እንዲሁም የወረርሽኝ ስርጭት ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት በፍጥነት እየጨመረ መምጣቱ ነው የተገለፀው፡፡

በአሜሪካ ብቻ ከ 1ሚሊዮን በላይ መድረሱን ጥናቱን ያጠኑት የዩንቨርሲቲው ሳይቲስቶች አረጋግጠው፣ በአሜሪካም ያለው የኮቪድ 19 ስርጭት ያዘገመ ቢመስልም ልክ እንደ አውሮፓ እና ደቡብ አሜሪካ ወደ ቀጣዩ መዓበል ሲሸጋገር ጉዳቱ የከፋ ይሆናል በሚል ስጋት ውስጥ መሆናቸው ነው የተገለፀው፡፡

በተያያዘም በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ባለው ጦርነት ሳቢያ ወደ ፖላንድ እና ሮማኒያ በሚገቡ ስደተኞች ሳቢያ በሁለቱ ሃገራት ላይ ያለው የኮቪድ ስርጭት እየጨመረ እንደመጣ ከድህረ ገጹ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ረድኤት ገበየሁ
የካቲት 29 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.