ናይጄርያ ዜጎቼ ዩክሬን ሄደው ለመዋጋት እንዲመዘገቡ አልፈቅድላቸውም ብላለች፡፡

ዩክሬን ከሩሲያ የገጠማትን ጦርነት ለመመከት እንዲያስችላት በወታደርነት የሚሳተፉ ፍቃደኞችን እየመለመለች መሆኑን ተከትሎ ናይጄርያ ዜጎቼ በፍፁም እንዲዋጉ አልፈቅድላቸውም ማለቷ ተሰምቷል፡፡

የናይጄርያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የዩክሬን ኤምባሲ በሀገራችን እንዲህ ያለ እንቅስቃሴ ውስጥ መግባቱን ክዷል ብሏል፡፡

በርካታ ናይጄርያውያን ወደ ኤምባሲው ሄደው በጦርነቱ ለመዋጋት ፍቃዳቸውን ማሳየታቸውን ግን ኤምባሲው ቢያስታውቅም የናይጄርያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ግን የዩክሬን ኤምባሲ እንዲህ ያለ እንቅስቃሴ ውስጥ መግባቱን ክዷል፡፡

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባዩ እንደገለፁት በየትኛውም የአለም ክፍል ዜጎቻችን ቅጥረኛ ወታደር ሆነው እንዲዋጉ አንፈቅድም ፣ ሀሳቡንም እናወግዛለን ብለዋል፡፡

እንደ ቢቢሲ ዘገባ ምንም እንኳን ኤምባሲው ለመዋጋት ፍቃደኛ ከሆነ ከእያንዳንዱ ናይጄርያዊ ለቪዛና ለትኬት 1 ሺህ ዶላር መጠየቁን አንስቷል፡፡

ሴኔጋል በዩክሬን ለመዋጋት የሚመዘገቡ ፍቃደኞችን ካስጠነቀቀች ከቀናት በኋላ ነው ናይጄርያ ዜጎቿን ቅጥረኛ ወታደር እንዲሆኑ እንደማትፈቅድላቸው የገለፀችው፡፡

የዩክሬን ኤምባሲ ጦርነቱ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ሴኔጋልያውያን መመዝገብ ይችላሉ የሚለውን የምልመላ ጥሪ ከፌስቡክ ገፁ እንዲያነሳም ሴኔጋል ትዕዛዝ ሰጥታለች

ሔኖክ አስራት
የካቲት 29 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *