የሸገር ዳቦ ፋብሪካ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራው እንደሚመለስ ተገለፀ።

በስንዴ ዋጋ መጨመር ምክንያት አቅርቦቱ ቀንሶ የነበረው የሸገር ዳቦ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ወደ አቅርቦት ስራው እንደሚመለስ ተገልጿል።

ፋብሪካው ወደ ስራ እንዲመለስ በእያንዳንዱ ዳቦ ላይ የከተማ መስተዳድሩ 1 ብር ከ 14 ሳንቲም ድጎማ ማድረጉን የተገለፀ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ በአመት 613 ሚሊየን ብር ድጎማ እንደሚያደርግ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ መስፍን አሰፋ ናቸው የገለፁት።

ከዚህ ሳምንት ጀምሮም በ 2ብር ከ 10 ሳንቲም መከፋፈሉን እንደሚቀጥል ተገልጿል።

መንግስት ካደረገው ድጎማ በተጨማሪ የተወሰነ የዋጋ ማሻሻያ በማስፈለጉ ከዚህ በፊት ይቀርብበት ከነበረው የዋጋ መጠን ጭማሪ ተደርጎ ወደ ማከፋፈል ሂደቱ እንደሚገባ ተገልጿል።

ፋብሪካው ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ወደ ምርት ሂደቱ በመግባት በቀን ከ700 እስከ 800 ሺህ ዳቦ በማምረት በአዲስ አበባ እና ዙሪያው ባሉት ከ400 በላይ ሱቆቹ ምርቱን ያከፋፍላል ተብሏል፡፡

እስከዳር ግርማ
የካቲት 29 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *