ጤና ሚኒስቴር የዘንድሮ አለም አቀፍ የሴቶች ቀንን የማህፀንና የጡት ካንሰር ምርመራ እና የደም ልገሳ በማድረግ አክብሯል፡፡

ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ “እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ” በሚል መሪ ቃል አለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አክብሯል፡፡

በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገነኙት በጤና ሚኒስቴር የእናቶች እና ህፃናት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር መሰረት ዘላለም እንዳሉት፣ በጤናው ዘርፍ የሴቶች ተሳትፎ አሁን ላይ ቀደም ሲል ከነበረው የተሸለ ቢሆንም አሁንም ገና ብዙ መሰራትን የሚጠይቅ ነዉ ብለዋል፡፡

በተያያዘም በተለያየ አጋጣሚ እና ሁኔታ የሴቶች ጥቃት አሁንም መኖሩን በማንሳት የዋንስቶፕስ (የአንድ መስኮት አገልግሎትን) የማብዛት እቅድ እንዳለም ተናግረዋል።

ይህም ተፈናቃይ በሚበዛባቸው አካባቢዎች እና በተለያዩ ቦታውዎች ጥቃት ተፈፅሞባቸው የሚመጡ ሴቶችን ህክምናን ጨምሮ የስነ-ልቦና ድጋፍ እና የህግ አገልግሎት በቀላሉ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ብለዋል ዳይሬክተሯ።

በአከባበር ስነ-ስርዓቱም ላይ የማህፀንና የጡት ካንሰር ግንዛቤ ፈጠራና ምርመራ እንዲሁም የደም ልገሳ ተደርጓል።

ከዚህም በተጨማሪ በየአካባቢው ተፈናቅለው ለሚገኙ ሰዎች የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች አልባሳት እና የማይበላሹ ምግቦች ተሰባስቧል።

የዘንድሮው የሴቶች ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ111 በኢቲዮጵያ ደግሞ ለ46 ጊዜ እየተከበረ ይገኛል።

በረድኤት ገበየሁ

የካቲት 29 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *