የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአየር እና የባሕር ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ከጅቡቲ ጋር ተፈራረመ


አየር መንገዱ ከኤር ጅቡቲ እና ከጅቡቲ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ኦፕሬሽን (ዲፖ) ጋር በመተባበር የባህር አየር መልቲሞዳል ትራንስፖርት መጀመሩን ነው ያስታወቀው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የባሕር እና አየር ሁሉን በአንድ የሆነ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን የጋራ ስምምነት ከጅቡቲ ዓለም ዐቀፍ የኢንዱስትሪ ፓርኮች አገልግሎት ( ዲፖ) እና ከጅቡቲ ኤር ጋር ተፈራርሟል።

ስምምነቱ ከቻይና በባሕር ወደ ጅቡቲ የሚመጡ ጭነቶችን የአየር መንገዱን ሰፊና ዘመናዊ የካርጎ ጭነት አገልግሎት አቅም በመጠቀም ከጅቡቲ ዓለም ዐቀፍ አየር ማረፊያ ወደ ተለያዩ የአፍሪካ አገራት በአየር ለማጓጓዝ የሚያስችል መሆኑን ዥንዋ ዘግቧል፡፡

በዘገባው እንደተመላከተው ከሆነ የኢትዮጵያ መንግስት የምስራቅ አፍሪካን ኢኮኖሚያዊ የእድገት ጉዞ ለማስቀጠል የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ዘርፉን እንደ አቅጣጫ መቀየሪያ ወስድዋል ይላል፡፡

በቅርቡም የ10 አመት የትራንስፖርት ዘርፍ ልማት እቅድ አውጥቶ የበርካታ የመንገድ እና የባቡር ፕሮጀክቶች ግንባታን የሚያሳይ እነደሆነ ተጠቁሟል።

የካቲት 30 ቀን 2014
ረድኤት ገበየሁ

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *