ዩክሬን ኃይሏን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተልዕኮዎች ልታስወጣ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ዩክሬን ከሩሲያ ጋር እያደረገች ላለው ውጊያ አቅሟን ለማጠናከር በአፍሪካ እና በአውሮፓ ፤ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ የሚገኙ ወታደሮቿን ፤ ትጥቅዋን እና ሄሊኮፕተሮችን ልታስወጣ ነው ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

የዩክሬን መገናኛ ብዙሃን እንዳስታቀው ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በተባበሩት መንግስታት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ ያሉ የዩክሬን ወታደሮች እና መኮንኖች ወደ አገራቸው በመመለስ ከሩሲያ ጋር የገጠሙትን ጦርነት እንዲቀላቀሉ ትእዛዝ ሰጥተዋል ብሏል፡፡

ትልቁ የዩክሬናውያን ወታደራዊ ኃይል በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ ሞኑጎ ውስጥ እያገለገሉ ሲሆን፤
ሌሎች ዩክሬናውያን በማሊ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ቆጵሮስ እና ኮሶቮ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ተልዕኮዎች ለመወጣት በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ ይገኛሉ ።

ይሁን እንጂ የዩክሬን መንግስት ባቀረበው ጥሪ መሰረት ወታደሮቹ ትጥቃቸውን እና ሄሊኮፕተሮችን ይዘው ወደ ዩክሬን ሊመለሱ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።

መሳይ ገ/መድህን
የካቲት 30 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *