የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ አሜሪካ በዩክሬን ስታካሂደው የነበረውን የላብራቶሪ ምርምር በይፋ እንድታጋልጥ ጠየቁ፡፡

ለሚካሄደው ድርድር ወደ ቱርክ ያቀኑት ላቭሮቭ በሰጡት መግለጫ ‘‘ስለምንጠይቀው መረጃ ዩክሬንም ሆነ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃው እንደሌላቸው እናውቃለን” ብለዋል፡፡

አሜሪካ ዩክሬን እና ሩስያ በሚዋሰኑበት ድንበር ላይ ባይሎጂካል መሳሪያዎችን የሚያለማ ላብራቶሪ አቋቁማ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ላቭሮቭ በሩስያ እና በቻይና ላይ ተመሳሳይ ሴራዎች ሲከወኑ ቆይተዋል ያሉ ሲሆን ከቀናት በፊት የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተመሳሳይ መረጃ መጠየቁም አይዘነጋም እንደ አር ቲ ዘገባ፡፡

ላቭሮቭ ይህ ወታደራዊ ተልእኮ በከፍተኛ ሚስጥር ሲካሄድ ቆይቷል ብለው፤ ለሩስያ ከፍተኛ የብሄራዊ ደህንነት ስጋት ነው ሲሉም ገልፀውታል፡፡

ጠዋት ላይ ዋይት ሃውስ ሩሲያ የኬሚካል ጥቃት ልትፈጽም ትችላለች ሲል መግለጫ ማወጣቱ የሚታወስ ነው፡፡

ሩሲያ በዩክሬን የኬሚካል ወይም የባዮሎጂካል መሳሪያ ጥቃት ልትፈጽም ስለምትችል “ሁላችንም ልንጠነቀቅ ይገባል” ሲል ዋይት ሃውስ አስታወቋል፡፡

ሩሲያ ስለ አሜሪካ የባዮሎጂካል መሳሪያ ቤተ ሙከራዎች እና በዩክሬን የኬሚካል ጦር መሳሪያ እያበለጸገች ነው ስትል የምትገልጸው የተሳሳተ ነው ሲሉ የነጩ ቤት ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ ገልጸዋል ።

የሐሰት መረጃዎቹ ተጨማሪ ምከንያት አልባ ጥቃቶችን ለማስረዳት መሞከሪያ “ግልጽ ዘዴ” ነው ሲሉ ጠርተውታል ሲል ቢቢሲ ነው የዘገበው።

አብዱሰላም አንሳር
መጋቢት 01 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *