የአለም ባንክ ባወጣው መረጃ መሰረት አፍሪካዊቷ ሀገር ደቡብ አፍሪካ ያልተመጣጠነ የሀብት ደረጃ ያለባት ሀገር ተብላለች፡፡
በዚህም ከ164የአለም ሀገራት ያልተመጣጠነ የሀብት ክፍፍል ካለባቸው ሀገራት በቀዳሚነት ተቀምጣለች፡፡
ለዚህ በምክንያትነት የተቀመጠው ጉዳይ ደግሞ የዘር የበላይነት በሀገሪቱ እጅጉን በመስፋፋቱ ነው ተብሏል፡፡
የአፓርታይልድ ስርአት ከሀገሪቱ ከተወገደ 30 አመታት ቢቆጠሩም የነጮች የበላይነት ሀገሪቷ አሁንም እየተፈታተናት እንደሚገኝ ነው አልጀዚራ ያስነበበው፡፡
በሀገሪቱ የሀብት አለመመጣጠን ተከትሎ የትምህርት ፍላጎቱ ከ30 በታች እንዲሆን ምክንያት መሆኑንም ተነግሯል፡፡
ደቡብ አፍሪካ ከገቢ አለመመጣጠን ጋር በተያያዘ ስሟ በተደጋጋሚ የሚነሳ ሀገር መሆኗ አይዘነጋም፡፡
በሀገሪቱ በተመሳሳይ የስራ አይነት እና ደረጃ ላይ የሚገኙ ሴቶች ከወንዶች 30 በመቶ ቅናሽ ይከፈላቸዋል ይላል የአለም ባንክ ያወጣው መረጃ፡፡
በደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ ተወገደ ቢባልም አሁንም ጓዙን ጠቅልሎ አለመውጣቱን መረጃዎች ይጠቁማሉ፤ ለዚህም አብዛኛው የሀገሪቱ የእርሻ መሬቶች የተያዙት በነጮች እጅ መሆኑን ነው፡፡
ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘም ሌላኛዋ አፍሪካዊት ሀገር ናሚቢያ 70 ከመቶ የሚሆነው መሬቷ አሁንም በነጮች እጅ ይገኛል ሲል የአለም ባንክ መረጃ ይጠቁማል፡፡
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 01 ቀን 2014 ዓ.ም











