8 ነፍሰጡር እናቶች በሕክምና ማጣት ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በሪፖርቱ ገለጸ፡፡

በአማራ ክልል መቄት ወረዳ ሸሆድ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በደረሰበት ዘረፋ እና ውድመት ምክንያት አገልግሎት መስጠት በማቆሙ በወረዳው 8 ነፍሰጡር እናቶች በሕክምና ማጣት ሕይወታቸው ማለፉን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ በአማራ እና በአፋር ክልሎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ ባወጣው ሪፖርት በአጠቃላይ 749 ያህል ዜጎች መሞታቸውን ገልጿል፡፡

አሸባሪው የህውሃት ቡድን በክልሉ በጤና እና በትምህርት ተቋማት ላይ በደረሰው ዝርፊያ፤ ውድመት እና ቃጠሎ የአካባቢው ነዋሪዎች የጤና እና ትምህርት አገልግሎት ማግኘት እንዳይችሉ ያደረገ ሲሆን፣ ነፍሰጡር እናቶች በሕክምና እጦት ሕይወታቸው አልፏል ሲል በሪፖርቱ አስታውቋል፡፡

የሕክምና ተቋማት በመውደማቸው እና በመዘረፋቸው በቂ ሕክምና ለማግኘት ሳይችሉ ሕይወታቸው ያለፈ ሕፃናትም አሉ ተብሏል።
በአማራ እና በአፋር ክልሎች የአሸባሪው የህውሀት ሀይሎች ባደረጉት የቡድን የአስገድዶ መድፈር ጥቃት በ100ዎች የሚቆጠሩ ሴቶች የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው ተጎጂዎች የደረሰባቸው ወሲባዊ ጥቓት በማህበረሰቡ ከታወቀ ሊደርስባቸው የሚችለውን መድሎ እና መገለል በመፍራት ብዙውን ጊዜ ጉዳታቸውን ለመናገር የማፈልጉ በመሆናቸው የጥቃቱ ስፋት በሪፖርቱ ከተጠቀሰው በላይ ሊሆን የሚችልበት አጋጣሚ ሰፊ ነው ሲል በዛሬው እለት ይፋ ባደረገው ሪፖርት አስታውቋል፡፡

መጋቢት 02 ቀን 2014 ዓ.ም
ሔኖክ ወልደገብርኤል

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *