በህገወጥ መንገድ ገበያ ላይ ሲሸጡ የተገኙና ግምታቸው 21 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ የሲጋራ ምርቶች እንዲወገዱ መደረጉን ሰምተናል
በሃገር ውስጥ ገበያ እንዳይሸጡ የተከለከሉ፤ በህገ ወጥ መንገድ በግለሰቦች ሱቆች ተገኝተው የተሰበሰቡ የሲጋራ ምርቶች እንዲወገዱ መደረጉን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምግብ እና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ነው የሰማነው።
ሻምላ እና ሬድ ስሜል የተባሉት የቱርክ እና የየመን ምርት የሆኑት እዚህ ሲጋራዎች በኮንትሮባንድ ገብተው በሱቆች ሲሸጡ እንደነበር እና በማህበረሰቡ ጥቆማ እንደተሰበሰቡ ተገልጿል።
ሲጋራዎቹ በይዘታቸው በጣም ከባድ ከመሆናቸው የተነሳ በውስጣቸው 250 የሰዎችን ጤና አደጋ ላይ የሚጥሉ ኬሚካሎች ከመያዙም በላይ፤70 በመቶ የሚሆኑት ተጠቃሚዎችን ለካንሰር በሽታ የሚመሩት ናቸው ብለዋል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምግብ እና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ትግስት በዳዳ ፡፡
አዲስ አበባን ከትንባሆ ጭስ ነጻ ለማድረግ እየሰራን ነው ብለዋል የከተማው ምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባስልጣን ምክትል ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ትዕግስት በዳዳ፡፡
መሳይ ገ/መድህን
መጋቢት 05 ቀን 2014 ዓ.ም











