ቻይና በሩሲያና ዩክሬን ጉዳይ ላይ ግልጽ የሆነ አቋሟን እንድታሳዉቅ እፈልጋለሁ ብላለች፤አሜሪካ፡፡

የአዉሮፓ ህብረትና አሜሪካ በግልጽ ለዩክሬን የተለያዩ ወታደራዊ ቁሳቁሶች እና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ላይ ሲሆኑ ቻይና በአንጻሩ ድጋፏ ለሩሲያ መሆኑ ይነገራል፡፡

ከሰሞኑም የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ቁልፍ የጸጥታ አማካሪ ፤ ከቻይናዉ ፕሬዝዳንት ሽ ጅንፒንግ የቅርብ ሰዉ ጋር መምከራቸዉ ተነግሯል፡፡
ዋና አላማዉም ቻይና ያላት ድጋፍ ለሩሲያ እንደሆነ ቢታወቅም ይህን አቋማን በግልጽ እንድታሳዉቅ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ይህም አሜሪካ አንዱ በቻይናም ሆነ በሩሲያ ላይ ተጽዕኖ የማድረጊያ መንግድ አድርጋ ወስደዋለች ተብሏል፡፡
የቻይናዉ ፕሬዝዳንት ሽ ጅንፒንግ በሩሲያና ቻይና መካከል ያለዉ ግንኙነት ጠንካራና ሁሉንም ያካተተ ገደብ የለሽ ነዉ ሲሉ መደመጣቸዉ በአሜሪካ ዘንድ ስጋትን ፈጥሯል፡፡

ይህ አገላለጽ ወታደራዊ ድጋፍንም ሊጨምር ይችላል በማለት አሜሪካና የአዉሮፓ ህብረት አባል ሃገራት መሪዎች ስጋታቸዉን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡
ለዚህም ይመስላል ቻይና ግልጽ የሆነ አቋሟን እንድታሳዉቅ አሜሪካ እየወተወተች የምትገኘዉ፡፡

ቢቢሲ
ሙሉቀን አሰፋ

መጋቢት 05 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.