በሁለት ቀናት ውስጥ ብቻ አምስት ድንገተኛ አደጋዎች መከሰታቸው ተነገረ፡፡

በአዲስ አበባ ቅዳሜ እና እሁድ አምስት ያህል ድንገተኛ አደጋዎች ተከስተው ከ150ሺህ ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

የመጀመርያ አደጋ የደረሰው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ አካባቢ በአንድ መኖር ቤት የደረሰ የጎርፍ አደጋ ሲሆን ሁለተኛ አደጋ የደረሰው ደግሞ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ አምስት ሜክሲኮ ቡናና ሻይ ህንጻ ላይ ሊፍት ወይም አሳንሰር ሲጠቀሙ የነበሩ ደንበኞች መብራት ጠፍቶ ሊፍት ውስት 30 ያህል ደቂቃዎች ካሳለፉ በኃላ ከሊፍቱ ሊወጡ ችለዋል፡፡

ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዘብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ አሳንሰር ወይም ሊፍት የሚያስጠቀሙ ተቋማት ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው ብለዋል፡፡

ከዚህ በፊት የመብራት አገልግሎት ጠፍቶ ሊፍት ሲጠቀሙ የነበሩ ደንበኞች ሕይወታቸው ያለፈበት ጊዜ እንደነበረ በማስታውስ ባለሙያው ምክራቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ሶስተኛ አደጋ ደግሞ የደረሰው በልደታ ክፍለ ከተማ ወራዳ አራት በሶስት ንግድ ሱቆች ላይ የደረሰ የእሳት አደጋ ነው፡፡

በኮልፌ ክፍለ ከተማ ወራዳ 15 አወልያ አካባቢ በሚገኝ አንድ መኖርያ ቤት ላይ የደረስ የእሳት አደጋ በከተማዋ የደረሰው አራተኛ አደጋ መሆኑን አቶ ንጋቱ ነግረውናል፡፡

ሌላኛው የእሳት አደጋ የደረሰው በአራዳ ክፍለ ከተማ ወራዳ አራት ዮሀንስ አካባቢ በሚገኝ መኖርያ ቤት ላይ የደረሰ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ነበር ተብሏል፡፡

በአደጋዎቹ አንድ ግለሰብ የመቁሰል አደጋ የደረሰበት ሲሆን በአጠቃላይ 27 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ንብረት መታደግ ተችሏል ሲሉ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ሔኖክ ወ\ገብርኤል
መጋቢት 12 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.