ኢትዮጵያ ውድድሩን በ4 ወርቅ 2 ብር እና 3 የነሐስ ሜዳሊያዎች በድምሩ በ9 ሜዳሊያዎች አሜሪካ እና ቤልጅየምን በማስከተል በአንደንነት አጠናቃለች።
ኢትዮጵያ በቤልግሬዱ 18ኛው የዓለም የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ያስመዘገበችው ውጤት ከእስከዛሬው ሁሉ የላቀ ሆኖ ተገኝቷል።
ኢትዮጵያ በውድድሩ ሜዳሊያ ያስመዘገበችባቸው ርቀቶች ፡ – የ1,500 ሜ ወንዶች ሳሙኤል ተፈራ – ወርቅ – 3:32.77 (የሻምፒዮናው ሪከርድ)- በ3000ሜ ወንዶች ሃገራችንን ወክለው የተሳተፋት ሰለሞንና ለሜቻ ተከታትለው በመግባት የወርቅ እና የብር ሜዳልያዎችን አሸንፈዋል ።
ሰለሞን ባረጋ በ7:41.38 ወርቅ ..ለሜቻ ግርማ በ7:41.63 ብር – 1,500 ሜ ሴቶች ከ1ኛ – 3ኛ ተከታትለው ገብተዋል ፡፡ ጉዳፍ ጸጋይ 3:57.19 (CR) 1ኛ ሆና ወርቅ( የሻምፒዮኑ ሪከርድ ሰዓት) አክሱማዊት እምባዬ 4:02.29 በሆነ ጊዜ 2ኛ ሆና ብር ፣ ሂሩት መሸሻ 4:03.39 በሆነ ጊዜ 3ኛ በመሆን ነሃሱን ተከታትለው ገብተው ሜዳልያውን ጠራርገውታል።
– የሴቶች 3,000 ሜ የዓለም የቤት ውስጥ ፍፃሜ ውድድር ፣ ለምለም ኃይሉ ወርቅ ፣ እጅጋዬሁ ታዬ ነሃስ- በ800 ሜ ሴቶች ፍረወይኒ ኃይሉ 2ኛ በመሆን የብር ሜዳልያውድድሩን በሁለተኛነት ያጠናቀቀቅችው አሜሪካ 3 የወርቅ ፣ 7 የብር እና 9 የነሐስ በድምሩ 19 ሜዳሊያዎችን እንዲሁም ቤልጂየም በ2 የወርቅ ሜዳሊያዎች በሶስተኛነት አጠናቃለች።
በውድድሩ የረዥም ጊዜ የኢትዮጵያ ተቀናቃኝ የነበረችው ኬኒያ በ 1 የብር እና በ1 የነሐስ ሜዳሊያዎች በ22ኛነት አጠናቃለች። ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው በ2008 በተደረገው 12ኛው የቫሌንሽያ የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና 4 ወርቅ፣ 1 ብር፣ 1 ነሃስ ያመጣችበት እንዲሁም በ2018 በተካሄደው 17ኛው የበርሚንግሃም የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና 4 ወርቅ፣ እና 1 የብር ሜዳሊያ ያስመዘገበችባቸው ከፍተኛ ውጤት ተብሎ የሚጠቀሱ ናቸው።
አቤል ጀቤሳ
መጋቢት 12 ቀን 2014 ዓ.ም











