በህወጥ መንገድ ወደ ጅቡቲ የሚያቀኑ የፍልሰተኞች ቁጥር አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን ኢትዮ ኤፍኤም ሰምቷል፡፡


በሱማሌ ክልል ሲቲ ዞን የምትገኘው አይሻ ወረዳ በህገወጥ መንገድ ወደ ጅቡቲ መተላለፊያቸውን ለሚያደርጉ ህገወጥ ፍልሰተኞች መተላለፊያ ሆናለች፡፡

የፍልሰተኞች ጉዳይ እለት ተእለት እየተበራከተ መቷል ሲል ቅሬታውን የነገረን የአይሻ ወረዳ ሰለምና ፀጥታ ቢሮ የፍልሰተኞች ጉዳይ ውወቅት ጠብቆ የደበዘዘ ቢመስልም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን ህገ-ወጥ ፍልሰተኞች በወረዳው መበራከታቸውን አስታውቋል፡፡

የአይሻ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ የቢሮ ሃላፊ አቶ ጃማ ሰኢድ ለኢትዮ ኤፍኤም እንደተናገሩት ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ በአንድ ተሸከርካሪ አማካኝነት ከ ተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች በወረዳው በኩል ወደ ጅቡቲ ለማቅናት ሲሞክሩ የነበሩ 32 ፍለሰተኞች አይሻ ወረዳ ላይ መያዛቸውን ነግረውናል፡፡

የወረዳው ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በሚያደርገው ቁጥጥር በየጊዜው ከሚይዛቸው ፍልሰተኞች ውጪ በሌሎች አማራጮች አቆራርጠው በህገወጥ መንገድ ወደ ጅቡቲ የሚያቀኑ እንዳሉም ነግረውናል፡፡

የድሬዳዋ ከተማ መስተዳደርን ጨምሮ ሌሎች የክልል ተቋማት ከልባቸው ሆነው ቢሰሩ ይህንን ችግር መቅረፍ ይችሉ ነበር የሚሉት ሃላፊው በተለይ የድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር ለጉዳዩ ምንም ትኩረት እንዳልሰጠው ነግረውናል፡፡

የጅቡቲ መንግስት በተለያዩ ሁኔታዎች በህገወጥ መንገድ የሚገቡትን ኢትዮጲያውያን ፍልሰተኞች በየቀኑ እየሰበሰበ ቢመልስም ፍልሰተኞቹ ተመልሰው የመሄድ ፍላጎታውን መግታት እንዳልተቻለና በዚህም የጅቡቲ መንግስት ለወረዳው ደጋግሞ ቅሬታ ማቅረቡን አንስተውልናል፡፡

መጋቢት 13 ቀን 2014 ዓ.ም
የውልሰው ገዝሙ

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.