ባለፉት ስድስት ወራት 12 ዜጎች በኤሌክትሪክ አደጋ ህይወታቸው ማለፉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የኤሌክትሪክ ስርቆት ለመፈጻም በሞከሩ ሰዎች ላይ እስከ ሞት ጉዳት እየደረሰ መሆኑን የአገልግሎቱ የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ ተናግዋል፡፡

ዳይሬክተሩ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ባለፉት ስድስት ወራት ከኤሌክትሪክ አደጋ ጋር ተያይዞ በ3ተኛ ወገን ላይ 12 ዜጎች ህይወታቸው ማለፉን እና 8 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት እንዲሁም 68 የንብረት ውድመት ማስከተሉንም ነግረውናል፡፡

ህጋዊ ስርአቱን ተከትሎ የኤሌክትሪክ አገልግሎቱን መጠቀም ሲገባ በህገወጥ መንገድ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘት በተደረገ ጥረት ይህ ጉዳት መከሰቱንም አቶ መላኩ ነግረውናል፡፡

የመሰረተ ልማት ስርቆት ላይ በተሰማሩ አካላትም ለመስረቅ በሚያደርጉት ሙከራ ውድ ህይወታቸውን እያጡ እንደሆነም ተግረውናል፡፡
ህብረተሰቡ እንዲህ ያሉ ድርጊቶችን እየተከላከለ ከራሱ ኪስ ወጥቶ የተገነባውን የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት እንዲጠብቅ አደራ ብለዋል፡፡

መጋቢት 13 ቀን 2014 ዓ.ም
አብድሰላም አንሳር

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.