ንግድ ቢሮው 2 ሺህ 165 የንግድ ተቋማት ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል


የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሆን ብለው የዋጋ ንረት ባስከተሉ 2 ሺህ 165 የንግድ ተቋማት ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን ቢሮው አስታውቋል።
የንግድ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆኑት አቶ ዳንኤል ሚኤሶ ለኢቲዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቁት ሆን ብለው ህዝቡን ለመበደል የተለያዩ ምርቶችን በመሰወርና የዋጋ ንረት እንዲከሰት ባደረጉ 2 ሺህ 165 የንግድ ተቋማት ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱ ተገልጿል።


በተጨማሪም በድንገተኛ የመጋዘን ፍተሻ ደግሞ 737 ሺህ 333 ሊትር ዘይት እና የተለያዩ የፍጆታ ምርቶች መያዛቸውን የነገሩን ሲሆን በህብረት ስራ ማህበራት በኩል ለህብረተሰቡ እንዲሰራጭ በማድረግ ለመንግስት ገቢ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

ገበያን ለማረጋጋትና የተከሰተውን የመሰረታዊ ምርቶች እጥረት ለመግታት ነዳጅን ጨምሮ እስከዚህ ወር ድረስ 1 ሚሊዮን 459 ሺህ ሊትር ዘይት ፤ 110 ሺህ 552 ኩንታል ስኳር ለማህበረሰቡ መሰራጨቱን አስታውቀዋል።

በተጨማሪም የነዳጅ እጥረት እንዳይከሰት 16 ሚሊዮን 416 ሺህ 375 ሊትር ሀገር ውስጥ ከገባው ነዳጅ ውስጥ 6 ሚሊዮን 148 ሺህ 514 ሊትር አዲሰ አበባ ውስጥ ባሉ ማደያዎች በኩል ማሰራጨት መቻሉን ሃላፊው አብራርተዋል፡፡

የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶችን በእሁድ ገበያ ለማዳረስ በተጀመረው ስራ እስከአሁን ድረስ 134 ሚሊዮን 795 ሺህ 400 ብር የሚገመት የተለያዩ ምርቶች መሰራጨታቸውንም አክለው ተናግረዋል፡፡

መጋቢት 13 ቀን 2014 ዓ.ም
ረድኤት ገበየሁ

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *