የአዉሮፓ ህብረት የአዉሮፓ ወታደራዊ የጦር ሃይል እንዲዋቀር ፍቃድ ሰጠ፡፡


የአዉሮፓ ህብረት በታሪኩ የመጀመሪያ ነዉ በተባለለት በዚህ ወታደራዊ የጦር ሃይል ማዋቀር ውሳኔ ላይ 5 ሺህ የሚሆኑ ጠንካራ ወታደሮችን ለማሰማራት እየሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የላቲቪያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኤድጋርስ ሪንኬቪችስ ይህ መነሳሳት የአዉሮፓ ህብረት ከኔቶ ጋር በመሆን ትክክለኛ የጂኦፖለቲካዊ መከላከል እና ደህንነት ላይ የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ የሚረዳዉ ነዉ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

የጉዟችን መጀመሪያ ነው ባሉት እቅድ በ 2020 ሲታሰብ ቀድመዉ ከነበሩ የአዉሮፓ ሃገራት ወታደራዊ የጦር ሃይሎቸ እና ከኔቶ ጋር በጋራ በመሆን በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ማጠናከሮችን እና ደህንነቱን ለማስጠበቅ ደግሞ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ታስቦ መጀመሩ አርቲ ኒውስ ነው የዘገበው፡፡

መጋቢት 14 ቀን 2014 ዓ.ም
እስከዳር ግርማ

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *