ሰነድ አልባ ስደተኞችን እንዳይቀጥሩ የደቡብ አፍሪካ መንግስት ትእዛዝ ሰጠ::

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት በሀገሪቱ የሚገኙ ኩባንያዎች ሰነድ አልባ ስደተኞችን እንዳይቀጥሩ፣እንዲሁም የሰራተኞቻቸውን ሰነድ በጥንቃቄ መመርመር እና መያዝ አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በደቡብ አፍሪካ ከ2.9 ሚሊዮን በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች እንደሚኖሩ የተነገረ ሲሆን ከነዚህ መካከል 10 ከመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው የተሟላ ሰነድ እንዳላቸው ተገልጿል፡፡

ከሰሞኑ በሀገሪቱ ጽንፍ የረገጡ ደቡብ አፍሪካዊያን ” መጤ “ ናቸው ባሉዋቸው የውጭ ሀገራት ዜጎች ከሀገራችን እንዲወጡ ሲሉ ተቃውሞ ማሰማት መጀመሩ ይታወሳል፡፡

በሀገሪቱ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ግንኙነት አላቸው የሚባሉት እነዚህ ዜጎች “ዱዱላ ንቅናቄ” እና “ዱዱላ ጆሀንሰበርግ “የሚል ቡድን አደራጅተው ተቃውሞአቸውን በመንግስት ላይ እያሰሙ የሚገኙት፡፡

እነዚህ ቡድኖች ዋነኛ ፍላጎታቸው በመጤዎች የተያዘው የንግድ ስርአት ለደቡብ አፍሪካ ዜጎች ይመለስ የሚል ነው፡፡
እንደዚሁም ” መጤዎች” ቀጥረው የሚያሰሩ በአነስተኛ ዋጋ ነው የሚሉት እነዚህ ቡድኖች በሀገራችን ሀብት የበይ ተመልካች መሆን የለብንም ይላሉ፡፡

የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት የቡድኖችን እንቅስቃሴ ለመቀልበስ እና ጥያቄያቸውንም በተወሰነ መልኩ መመለስ እንዲያስችላቸው የወሰኑት ውሳኔ ግን በበርካቶች ዘንድ ተቃውሞ ተነስቶበታል፡፡
አፍሪካ ሀገር ሆና ለአፍሪካዊያን ያልተመቸች ሀገር እያሉ በሀገሪቱ በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ስደተኞች ተቃውሞአቸውን የገለጹ ሲሆን ፕሬዝዳንቱ በሀገሪቱ የተጀመረውን ተቃውሞ ለማብረድ የወሰኑት ውሳኔ ሳያስቡት ሌላ መዘዝ አስከትሎባቸዋል ሲል የዘገባው አፍሪካ ኒውስ ነው፡፡

መጋቢት 14 ቀን 2014 ዓ.ም
ሔኖክ ወልደገብርኤል

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.