የኔቶ አባል ሀገር የሆነችው ፖላንድ ከሩስያ ጋር በተፈጠረው አለመግባባት የሩስያ ዲፕሎማቶችን በአምስት ቀናት ውስጥ ሀገሯን ለቀው እንዲወጡ ውሳኔ አሳልፋለች፡፡
ይህንንም ተከትሎ በፖላንድ የሩስያ አምባሳደር ሰርጌ አንድሪው ከፖላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኩል የተላለፈው ውሳኔ ፖላንድን ዋጋ ያስከፍላታል ብለዋል፡፡
በዛሬው እለት የፖላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እነዚህ ዲፕሎማቶች ሀገራችን ላይ ተቀምጠው እየሰለሉን ነበር፣ እንደዚሁም የዩክሬን ጦርነት ወደ እኛ እንዲዛመት በትኩረት እየሰሩ አግኝቻቸዋለሁ በሚል ምክንያት ከሀገራችን እንዲወጡ ውሳኔ ላይ የደረስነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በፖላንድ የሩስያ አምባሳደር ሰርጌ አንድሪው በበኩላቸው ፖላንድ በወሰደችው እርምጃ ልክ ሩስያም ተመጣጣኝ እርምጃ ፖላንድ ላይ ትወስዳለች ብለዋል፡፡
ሩስያ እና ዩክሬን ጦርነቱን ለማስቆም ጥርትእየተደረገ ባለበት ሰአት ፖላንድ የወሰደችው እርምጃ በእሳቱ ላይ ቤንዚን እንደመጨመር ነው ተብሏል፡፡
ምክንያቱም ፖላንድ የኔቶ አባል ሀገር መሆኗን ተከትሎ ሩስያ በፖላንድ ያልተመጣጠነ እርምጃ የምትወስድ ከሆነ አባል ሀገራቱ በጦርነቱ በቀጥታ የሚሳተፉበት አጋጣሚ ከፍተኛ ሊሆን ይችላል እየተባለ ይገኛል፡፡
እስከዚህ ሰአት ድረስ 10 ሚሊየን የሚጠጉ ዩክሬናዊያን ሀገራቸውን ጥለው ወደ ጎረቤት ሀገር ፖላንድ እና ሌሎችም ሀገራት ተሰደዋል ሲል የመንግስታቱ ድርጅት ያስታወቀው፡፡
መጋቢት 14 ቀን 2014 ዓ.ም
ሔኖክ ወልወደገብርኤል











