ሰሜን ኮርያ በአለም አቀፍ ደረጃ የተከለከለው ድንበር ተሸጋሪ ሚሳኤል መሞከሯ ተሰምቷል፡፡

ሰሜን ኮርያ በአለም የተከለከለው ድንበር ተሸጋሪ ሚሳኤል ሙከራ ያደረገችው ከ2017 ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ ነው ስትል ደቡብ ኮርያ ያስታወቀችው፡፡

ሰሜን ኮርያ የሞከረችው ይህ ሚሳኤል ለአለም ህዝብ አስደንጋጭ ዜና ነው በማለት ድረጊቱን አውግዛለች ፡፡
ሰሜን ኮርያ በተደጋጋሚ ወደ ምድር እና ባህር የምታስወነጭፋቸውን ሚሳኤሎች ተከትሎ ከአለም ማህበረሰብ እንደትገነጠል አድርጓታል፡፡

የሀገሪቷ ጸብ አጫሪ ድርጊት በመከታተል ትችቷን የምትሰነዝረው አሜሪካ አሁን ሰሜን ኮርያ ከሞከረችው የተከለከለ ድንበር ተሸጋሪ ሚሳኤል ተከትሎ ለጊዜው ምንም አላለችም፡፡

ሰሜን ኮርያ ከሰሞኑ በአንድ ወር ጊዜ ብቻ ከ10 በላይ ሚሳኤሎችን ማስወንጨፋ ነው የሲጂቲኤን ዘገባ የሚጠቁመው፡፡

መጋቢት 15 ቀን 2014 ዓ.ም
ሔኖክ ወልደገብርኤል

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *