በአዲስ አበባ ለ2.5 ሚሊዮን ህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ ያሉት 10ሺህ 500 ተሸከርካሪዎች ብቻ መሆናቸውን ሰምተናል በመዲናዋ ይትራንስፖርት ፍላጎት እና የተሸከርካሪው ቁጥር የሚጣጣም አለመሆኑ ተነግሯል፡፡


የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የኮሚኒኬሽን ዳሬክተር አቶ አረጋዊ ማሩ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በመዲናዋ እስከ 2013 ዓ.ም ድረስ በተመዘገበው ቁጥር መሰረት 630ሺህ ተሽከርካሪዎች ያሉ ሲሆን የታክሲ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙት ግን 8ሺህ 500 ያህሉ ብቻ ናቸው ብለዋል፡፡
በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት ከሚሰጡት የአንበሳ፣ የፐብሊክ እና ሸገር ባሶች ውጪ በትራንስፖርት ስራ ላይ የተሰማሩ ተሸከርካሪዎች ከ8ሺህ አይበልጡም ብለውናል፡፡

በዚህም የፍላጎት እና አቅርቦት አለመመጣጠን በከተማዋ እንዳለ ነው ዳይሬክተሩ የነገሩን፡፡
በመዲናዋ የሚገኙ ሌሎች ዜጎች ደግሞ የግል ተሽከርካሪዎቻቸውን እየተጠቀሙ እንዳሉም ነው የተነገረው፡፡
እንደ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር መረጃ፣

በኢትዮጵያ ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ተሸከርካሪዎች እንዳሉና ከእነዚህ ተሽከርካሪዎች መካከል ግማሽ ያክሎቹ የአገልግሎት ዘመናቸው ያለፈባቸው እንደሆኑ ተነግሯል፡፡

ሄኖክ ወልደገብርኤል

መጋቢት 15 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *