ከቀድሞ የዛምቢያ ሚኒስትር በሙስና ገዝተዋቸዋል የተባሉ ሆቴልና ሄሊኮፕተሮች ተያዙ

የቀድሞ የዛምቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆሴፍ ማላንጂ በህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
በቁጥጥር ስር የዋሉት ባለሥልጣኑ በወንጀል ተገዝቷል ተብሎ የተጠረጠረ ሆቴል እንዲሁም 700 ሺህ ዶላር አውጥተው ሄሊኮፕተር ገዥተዋል ተብሎም ተጠርጥረዋል።

ይሆን እንጂ ማላንጂ ከዚህ ቀደም ክሱን ውድቅ አድርገው እንደነበር ቢቢሲ አፍሪቃ አስታውሷል፡፡
በዛምቢያ የአደንዛዥ ዕፅ ማስፈጸሚያ ኮሚሽን (DEC) ፀረ-ገንዘብ ማሸሽ ክፍል ቃል አቀባይ ማቲያስ ካማንጋ እንደተናገሩት “ሆቴሉ ከሁለቱ ሄሊኮፕተሮች ጋር በቁጥጥር ስር ውሏል።

በአካባቢው የሚገኘው ዳይመንድ ቲቪ እንደዘገበው ምንም እንኳን ባላስልጣኑ በወንጀል በተገኘ ክስ ቢጠረጠሩም ፖሊስ በዋስ እንደለቀቃቸው ተዘግቧል።

ማላንጂ በነሐሴ 2021 በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በተሸነፈው በቀድሞው ፕሬዝዳንት ኤድጋር ሉንጉ ካቢኔ ውስጥ አገልግለዋል።

የዛምቢያ አዲሱ መንግስት ባለፈው አመት ምርጫን ካሸነፈ በኋላ የፀረ-ሙስና ዘመቻን እያቀጣጠለ ቢሆንም ቅሉ እስካሁን ምንም አይነት ከባድ የጥፋተኝነት ውሳኔዎችን ማረጋገጥ አልቻለም ብሏል ዘገባው፡፡

መጋቢት 15 ቀን 2014 ዓ.ም
ያይኔአበባ ሻምበል

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *